ይህ ታሪክ የዛሬ 20 ዓመት በፊት የተከሰተ ነው :: በዚያን ጊዜ የ 7ዓመት ልጅ ነበርኩ ::
በሰፈራችን ላይ በጦርነት ወቅት የጦር አዉሮፕላኖች ቦምብ ለመጣል ልምምድ ያደርጉ ነበር ::እያንዳንዱ ቦምቦች ሳይፈነዱ መሬት ዉስጥ የቀሩ ነበር :: በዚያን ጊዜ እኛ ሕፃናት እነዚህ ያልፈነዱ ቦምቦች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ አናውቅም ነበር :: እንደ መጫወቻ እየቆጠርናቸው እንጫወትባቸው ነበር ::
አንድ ቀን 4ወንዶች 1ሴት በድምሩ 5ልጆች ሆነን በ አንድ ያልፈነዳ ቦምብ እየተጫወትን ሳለ : በድንገት ፈነዳ :: በዚያን አስከፊ ፍንዳታ 2ወንዶች ልጆች ህወታቸዉን አጡ :: ሌላው 1ወንድ አይኑ ጠፋ ከባድ ጉዳት ደረሰበት ተጨማሪ 4,ተኛው ወንድ ቀላል ጉዳት ደረሰበት እኔም ከባድ ቁስለት ደረሰብኝ ::
ህይ ክስተት ህወቴን ለዘላለም ቀይሮታል ::ዛሬም ከ 20 ዓመት በህዋላ የዚያ ቀን ትዉስታ አሁንም በአእምሮዬ አለ ::
ይህ ታሪክ የማካፍለው ጦርነት በሕፃናት ላይ የሚያስከትለዉን መራራ ዉጤት እንዳንረሳ ነው ::ያልፈነዱ ፈንጅዎችና ቦምቦች ከጦርነት በህዋላም ለ አመታት የሠዎችን ሂወት ሊያጠፋ ይቻላሉ :: ሕፃናት ከእነዚህ አዳጋዎች እንዲጠበቁ የማስተማር የማስወገድ ሥራ በጣም አስፈላጊ ነው ::
የሰላም እና የቦምብ ጨዋታ :የ 20 ዓመት የህወት ጠባሳ የልጅነታችን ዓለም የምትለካው በምንጫወታቸው ጨዋታዎች ነበር ::ነገር ግን በሰፈራችን :የሰማዩ ድምፅ የጀትች ሆነ :የመሬቱ የቦምብ ማረፊያ በሆነበት ሁኔታ : ተልጅነት ትዝታችን ከደም እና ከብረት ጋር የተሳሰረ ሆነ ::
በዚያን ወቅት የጦር ጄት አብራሪዎች ስርማዩን እየስነጠቁ ለመለማመጃ የሚጥሉት ቦምብ የእኛ የዕለተ ተዕለተ ዉሎ ነበር :: በአየር ላይ የሚወረወሩት ቦንቦች ግማሾቹ ሲፈነዱ :ሌሎች ግን ሳይፈነዱ መሬት ላይ ተከባለው ይቀሩ ነበር ::አሻንጉሊት ወይም እንደ ዕቃ መጫወቻ እንቆጥራቸው ነበር ::የመንግስት ቦምብ እያልን ስንጠራቸው :አደጋነታቸው ሳይገባን አደግን ::
ከዕለታት አንድ ቀን :አምስት ሆነን ነበር የተሰበሰብነው __አራት ወንዶች እና እኔ :አንዲት ሴት ልጅ :: በዚያች ስዓት አምስታችንም ተምንቻወተው አደገኛ በሆነው “የሰላም ጊዜ የጦር መሳሪያ ” ነበር :: በእጃችን የነበረው ፈንጂ የያዘው ቦንብ ነበር ::
ድንገት :በሳቅ እና በጨዋታ ምሃል :ያ ቦምብ የለቀቀው ድምፅ የልጅነታችንን ዓለም በሰከዶች ዉስጥ የሞት ማርሽ ሆኖ ተገኘ :: በዚያን ቅፅበት ሁለት ጕደኞቼ ሂወታቸው አለፈ :: እኔ እና ሌላው አንድ ጕደኛዬ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰብን ::ሌላው አንድ ጕደኛዬ ቀላል ጉዳት ደረሰበት ::በሰዉነታችን ላይ የገባው ብረት ቁርጥራጭ :የፈጠረው ጠባሳ እና የዉስጥ ጉዳት የዘመናት ታሪክ ሆኖ ቀረ ::
ከዚያን ቀን በህዋላ ህይወቴ በሆስፒታል :በህክምና እና በህመም ተተካ ::ዛሬ 20 ዓመት አልፎታል : ምንም እንኩዋን የብረት ቁርጥራጭ ከሰዉነቴ ዉስጥ ቢወጣም :የዚያን ፍንዳታ መዘዝ ግን አሁንም በዉስጤ አለ ::ቁስሉን በጊዜው የማጠብ :የህመም ስሜቱ :እና የ 20 ዓመት በፊት የነበረዉን ያንን አስከፊ ቀን ያስታዉሰኛል ::
ከአምስቱ ጕደኞቼ መካከል ተርፈ :በሕይወት ጎዳና ላይ እየተጕዝሁ ያለሁት የጦርነትን አዳጋ ለሌሎች ለማሳየት ነው ::ቦምብ አሻንጉሊት አይደለም የይኛዉም ቦምብ ቢሆን :ሳይፈነዳ ቢቀር እንኳን : የመግደል አቅሙ በዉስጡ ታፍኖ የሚኖር የስዓት ቦምብ ነው ::
ታሪኬ የብዙዎች ድምፅ ነው :: ያደግንበት የጨዋታ አዉድማ :የሞት አዉድማ ነበር ::ዛሬም ቢሆን :ያልፈነዱ መሳሪያዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደረሱት አዳጋ ይቆም ዘንድ :ዓለም ይህን ታሪኬን እንዲያስታዉስ እሻለሁ ::
